
"ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ"
ይህ ለረጅም ጊዜ ሲመኙት የነበረው ቅድስት አገር ኢየሩሳሌምን
የመጎብኘት ታሪክ ዐድል አያምልጥዎ፤
እያለ የሠላም ጉዞ ወኪል ጥሪውን ያቀርባል፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ፤
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጸነሰባትን፤ የተወለደባትን፤ ልዩ ልዩ ገብረ ተአምራት የፈጸመባትን፤
ሥራዓተ ጥምቀት ያካሄደባትን፤ ሞትና ድል አድርጎ በክብር የተነሳባትን፤ ያረገባትን፤ ብርሃነ መለኮቱን
የገለጸባትን ቅድስት አገር ኢየሩሳሌምን ይጎበኙ ዘንድ ታላቅ ታሪካዊና መንፈሳዊ ጥሪ ቀርቦልዎታል፤
ይህም አጋጣሚ ኢትዮጵያ በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ያላትን የታሪክና የቅድስና ይዞታዎቿን
ከመላው ዓለም የሚመጡት ማዕመናን እንዲያዩትና እንዲያውቁት አመች ወቅት በመሆኑ
ይህንን ተስማሚ የጉብኝት ዕለት ማደራጀቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
መጪውን የትንሣኤ በዓል በሀገር ቅድስት ኢየሩሳሌም ለማክበር ለምትፈልጉ ምዕመናን ልዩ የጉዞ፣
የሆቴልና የጉብኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ዝግጅቱ ሆቴልን፣ምግብንና ጉብኝትን ያጠቃልላል።
ምዕመናን ጋር አብረው በመጓዝ ታሪካዊዋን ቅድስት ከተማ፣ ቅዱሳት ገዳማትና አካባቢዋን
መጎብኘት እንዲችሉ በስልክ ቁጥር 310-649-5030 ደውለው ሰላምን ያነጋግሩ።